ሶማሌላንድ የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ ትፈልጋለች 01.05.2024
የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ንብረት የሆነው ዱባይ ወርልድ ኩባንያ የሚያስተዳድረው የበርበራ ወደብ የኢትዮጵያን 30 በመቶ ጭነት እንዲያስተናግድ የሶማሌላንድ ባለሥልጣናት አቅደዋል። ለዚህም የወደብ አጠቃቀም እና የጉምሩክ ሥርዓቶችን የተመለከተ ሥምምነት በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል መፈረም አለበት። ሥምምቱ በሚቀጥሉት 60 ቀናት ሊፈረም እንደሚችል የሶማሌላንድ የወደቦች አስተዳደር ባለሥልጣን ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።